የዓለም ወጣቶች ቀን በሐዋሳ ከተማ ተከበረ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ወጣቶች ቀን በሐዋሳ ከተማ ተከብሯል፡፡
ቀኑ የተከበረው÷ “የወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንትናዊ ሰላም” በሚል መሪ ሐሳብ ነው፡፡
በአከባበሩ ላይም አርቲስቶችና ጋዜጠኞችን ጨምሮ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
ከዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ጋር በተያያዘ በትናንትናው እለት የደም ልገሳ ተደርጓል፡፡
በዕለቱም ከ100 ዩኒት በላይ ደም መሰብሰቡን የሐዋሳ ደም ባንክ አገልግሎት ስራ አስኪያጅ ተሻለ ጨበራ ተናግረዋል።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ጸጋዬ ቱኬ (ረ/ፕ)÷ ከተማዋን የቱሪስት መዳረሻ ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
የኪነ- ጥበብ ቤተሰቦችም ከተማዋን በማስተዋወቅ የቱሪዝም ማዕከል እንድትሆን የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በዕለቱ የማስ ስፖርት፣ የተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት እና በታቦር ተራራ ላይ የችግኝ ተከላ መርሐ- ግብር ተከናውኗል።
በጥላሁን ይልማ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!