Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል ለቀጣዩ የትምህርት ዘመን የትምህርት ግብዓት እየተሠራጨ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል መስከረም 2 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚጀመረው የትምህርት ዘመን የትምህርት ግብዓትና መሠረተ ልማት የማሟላት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው የሥርዓተ-ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክተር ወልዶ ሀይሠማ እንዳሉት፥ በ2016 የትምህርት ዘመን በክልሉ ከ290 ሺህ በላይ ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ለተማሪዎቹ ከ1 ሚሊየን 500 ሺህ በላይ መጽሐፍት እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው፤ ከዚህ ውስጥ 168 ሺህ ታትመው ወደ ትምህርት ቤቶች መሠራጨታቸውንም ነው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት።

በተጨማሪም የ562 ሺህ 633 መጽሐፍት ኅትመት ተጠናቆ ከመስከረም ወር በፊት ወደ ትምህርት ቤቶች እንዲደርስ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ቀሪ ከ700 ሺህ በላይ መጽሐፍት ደግሞ ከመስከረም ወር በኋላ ታትመው እንዲሰራጩ ይደረጋል ነው ያሉት።

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.