Fana: At a Speed of Life!

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ለ40 ሺህ ዜጎች ነፃ የሕክምና አገልግሎት ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል “በጎነት ለጤናችን” በሚል መሪ ሃሳብ ለ40 ሺህ ዜጎች ነፃ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታወቀ።

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የሕክምና ኮሌጅ የበጎ ፈቃድ አስተባባሪ ዶክተር ሙሉቀን ተስፋዬ፥ ከነገ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ነፃ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅቱ መጠናቀቁን ገልጸዋል።

በ2015 በጀት ዓመት ለ35 ሺህ ዜጎች ነፃ የሕክምና አገልግሎት መሰጠቱን አስታውሰው በተያዘው በጀት ዓመትም ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።

በመሆኑም ከነሐሴ 11 እስከ ነሐሴ 18 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ 40 ሺህ ለሚደርሱ የኅብረተሰብ ክፍሎች ነፃ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ታቅዷል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከጤና ተቋማት ጋር በመቀናጀት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች በሚሰጠው የህክምና አገልግሎት ከፍለው ለመታከም የማይችሉ፣ የጎዳና ተዳዳሪዎችና ለልዩ ልዩ በሽታዎች ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎት መሆኑን ጠቅሰዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.