ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በሴቶች ማራቶን የተመዘገበውን ድል አስመልክቶ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በሴቶች ማራቶን የተመዘገበውን ድል አስመልክቶ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ፕሬዚዳንቷ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ፥ በሴቶች ማራቶን ልጆቻችን አማኔ በሪሶ ወርቅ ፤ኀይተቶም ገብረሥላሴ ብር አመጡ! ድጋሚ ደስታ! አኮራችሁን! ሲሉ አስፍረዋል፡፡
በዚህምም ፥ ‘’መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ደስ አለን! ይህ ነው ሕዝባችን፤ ሁላችንም የምንጋራው፣ ብቃታችሁን ያሳየ የማያሻማ ድል! ይባርካችሁ!!’’ ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
#ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!