Fana: At a Speed of Life!

መከላከያ ሚኒስቴር አዲስ የተሸከርካሪ ሰሌዳ አገልግሎት ላይ አዋለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መከላከያ ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ሲጠቀምበት የነበረውን የተሽከርካሪ ሰሌዳ በአዲስ ሠሌዳ በመቀየር ከነሐሴ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት ላይ ማዋሉን አስታወቀ፡፡

የመከላከያ ሎጅስቲክስ ዋና መምሪያ ለተዋጊ ክፍሉ ግዳጅ አፈፃፀም ተጨማሪ አቅም የሚሆኑ ተሽከርካሪዎችን ለዕዞችና ለክፍሎች ቁልፍ አስረክቧል፡፡

የተሽከርካሪዎችን ቁልፍ ያስረከቡት የመከላከያ ሎጅስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጀኔራል አብዱራህማን እስማኤል÷ አመራሮች እና ባለሙያዎች ለንብረቱ ደህንነት ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጡ አሳስበዋል፡፡

በተለያየ ምክንያት የተቋሙ በርካታ ሠሌዳዎች ከተቋሙ እውቅና ውጪ በሌሎች እጅ መገኘቱ ለህገ-ወጥ ተግባር እንዳይውሉ ታሳቢ ተደርጎ ሠሌዳው መቀየሩንም አስታውቀዋል፡፡

በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሁሉም የተቋሙ ተሽከርካሪዎች አዲስ ሰሌዳ ይደርሳል ማለታቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

አሁናዊ የሠራዊቱን ተልዕኮ እና ግዳጅ መነሻ አድርጎ በሚሰጡት አገልግሎት መሰረት በኮድ ጭምር ተለይተው የተዘጋጁ መሆናቸውንም ነው የገለጹት፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.