Fana: At a Speed of Life!

ኪም ጆን ኡን ለጉብኝት ሩሲያ ገቡ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 1 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለጉብኝት ሩሲያ ገቡ።

ኪም ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን ጋር ለመነጋገር በባቡር ሩሲያ መግባታቸው ታውቋል።

በቆይታቸውም ከፑቲን ጋር በመሳሪያ ሽያጭ ጉዳይ ላይ ይነጋገራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከስፍራው የሚወጡ ዘገባዎች ያመላክታሉ።

የአሁኑ የእርሳቸው ጉብኝት አሜሪካ ፒዮንግያንግ ከሩሲያ ጋር በጦር መሳሪያ ጉዳይ እንዳትስማማ እያስጠነቀቀች ባለችበት ወቅት የተደረገ መሆኑም ነው የተገለጸው።

በጉብኝታቸው የሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ ወታደራዊ ሃላፊዎችን፣ የዘርፉ ኢንዱስትሪ መሪዎችን እና ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎችን አስከትለው መግባታቸውም ነው የተሰማው።

ሞስኮ ፒዮንግያንግ የጦር መሳሪያ እንድትሸጥላት ፍላጎት ያላት ሲሆን፥ በአንጻሩ ሰሜን ኮሪያ የምግብ እርዳታ እና ማዕቀብ ለተጣለበት የኒውክሌር እና ሚሳኤል ፕሮግራሟ ማዘመኛ የቴክኖሎጂ ድጋፍ ትሻለች መባሉን ሬውተርስ እና ቢቢሲ አስነብብዋል።

ክሬሚሊንም ሁለቱ መሪዎች በቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ማረጋገጯ ሰጥቷል።

 

ብዙም የውጭ ሃገር ጉዞ የማያዘውትሩት ኪም በፈረንጆቹ 2019 ነበር ለመጨረሻ ጊዜ ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር በአካል የተገናኙት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.