የኮቪድ -19 ወረርሽኝ የአዕምሮ ጤና ቀውስ ሊያስከትል ይችላል-ተመድ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በስፋት የስነልቦና ጭንቀት ሊያስከትል እንደሚችል አስጠነቀቀ።
ድርጅቱ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በብዙ ሰዎችበጭንቀት እና ብቸኝነት እንዲሰቃዩ በማድረግ የአእምሮ ጤንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ገልጿል።
ለዚህ በሽታ ይበልጥ ተጋላጭ በመሆን ከፊት መስመር ላይ የሚገኙት የጤና ባለሙያዎች ፣ ከሥራ ውጭ ያሉ ሠራተኞች ፣አረጋውያን ፣ በቤት ውስጥ ልጆቻቸውን በማስጠናት በውጥረት ውስጥ ያሉ ቤተሰቦች መሆናቸውን ነው ያመላከተው።
ከዚያም ባለፈ ብዙ ሀገሮች ለረጅም ጊዜ በአእምሮ ጤና ክብካቤ ላይ የሚያደርጉት ኢንቨስትመንት መቀነሳቸውንም ነው ድርጅቱ ያነሳው።
ስለሆንም ችግሩን ለመቅረፍ ሐሙስ በተለቀቀው የፖሊሲ ሰነድ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፥ አገራት ወረርሽኙን የመግታት እቅዶቻቸው ላይ የአእምሮ ጤና እና የስነልቦና ማህበራዊ ድጋፍ እንዲያካትቱ ጥሪ እያቀረበ እንደሚገኝም ነው የተገለጸው።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥሩ የአእምሮ ጤና ለሠራተኛ ማህበረሰብ ወሳኝ መሆኑን ጠቁሞ፥ እነዚህ እርምጃዎች ከሌሉ ዓለም የአካላዊ ጤንነት ቀውስ ብቻ ሳይሆን የአእምሮ ጤና ቀውስም ያጋጥማታል ነው ያለው።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!