Fana: At a Speed of Life!

የትምህርትን መሰረተ ልማት ማሻሻል የቀጣዩን ትውልድ የወደፊት እድል ማሻሻል ነው – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በተመድ ጉባዔ ላይ የትምህርትን መሰረተ ልማት ማሻሻል የቀጣዩን ትውልድ የወደፊት እድል ማሻሻል መሆኑን ገለጹ።

ሚኒስትሩ ተመድ ትምህርት በዲጅታል ዘመን ውስጥ ለልማት፣ ለፍትሃዊነት፣ ለሠላምና ለደህንነት የሚያግዝ ኢንቨስትመንት በሚል በኒውዮርክ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

በንግግራቸውም፥ በትምህርት ላይ ኢንቨስት ማድርግ ስለ ቀጣዩ ትውልድና ዓለም ኢንቨስት ማድርግ ነው በማለት ገልጸዋል።

እንደ ሀገርና መንግስት የተለያዩ ለውጦችን በትምህርት ላይ እያካሄድን እንገኛለንም ያሉት ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ ካላት ዓመታዊ በጀት 20 በመቶ ለትምህርት ስራ እንደመደበች ማንሳታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በጀቱ መንግስት ካለው አቅምና በትምህርት ዘርፉ ከሚስተዋለው ውስብስብ ችግር አንጻር በቂ አለመሆኑንም ነው የጠቆሙት፡፡

ይህን ተከትሎ በዚህ ዓመት የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ለማሻሻል ያለመ ‘ትምህርት ለትውልድ ‘ ሀገራዊ ነቅናቄ በመጀመር መላው ህብረተስብ የብኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ እየተደረገ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ትምህርት ስርዓት ውስጥ ካሉ ዋና ዋና ችግሮች መካከል በትምህርት ቤቶች ምቹ የመማሪያ አካባቢ አለመኖሩ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ንፁህ የመጠጥ ውሃ፣ ተገቢ የመጸዳጃ ቤት አገልግሎት፣ የቤተ ሙከራና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አቅርቦት የሚባሉት መሰረታዊ መገልገያዎች የሌላቸው መሆኑን አብራርተዋል።

በመድረኩም ትምህርትን በመዋዕለ ንዋይ መደገፍ እስካልተቻለ ድረስ የዘላቂ ልማት ግቦችን ማሳካት ወይም እየተከሰቱ ያሉ ቀውሶችን መፍታት እንደማይቻል ተገልጿል።

#Ethiopia #UN #Education

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.