Fana: At a Speed of Life!

ጉቴሬዝ ተመድ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ “ሰላም ፣ብልፅግና፣ ለውጥና ዘላቂነት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ከሚገኘው የተመድ 78ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ነው የተደረገው፡፡

በውይይታቸውም አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ጥልቅ የሆነ የአጋርነት ስሜት አንዳላቸው አውስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ያሉባትን የማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎች ለመፍታት እያደረገች ባለው ጥረት ስኬታማ እንድትሆንም ተመኝተዋል።

ተመድ ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ግንኙነት አጠናክሮ እንዲቀጥል በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ጠቁመው÷ኢትዮጵያ በባለ ብዙ ወገን የትብብር ስርዓት ቁልፍ ሚና ያላት ሀገር እንደሆነችም አንስተዋል፡፡

አቶ ደመቀ ተመድ እና ዋና ፀሐፊው በግል ጥረታቸው ለኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ወቅቶች ያደረጉትን ድጋፍ አድንቀዋል።

የሰላም ስምምነቱን ትግበራ አስመልክተው ለአንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጻ ማድረጋቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ተመድ የመልሶ ግንባታና መልሶ ማቋቋም ጥረቶችን እንዲሁም ሌሎች የሰብዓዊ ጉዳዮች ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.