Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በቻይና እየተካሄደ በሚገኘው የቡና ኤግዚቢሽን ላይ እየተሳተፈች ነው

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በቻይና ሀንጆ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የቡና ኤግዚቢሽን ላይ እየተሳተፈች ትገኛለች፡፡

በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ በፈረንጆቹ ከመስከረም 21 እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2023 በሚካሄደው “ኮፊ መንዝ ኦፍ ኤዥያ ጌም፣ ሀንጆ” በተሰኘ የቡና አውደ ርዕይ ላይ የመጀመሪያ ሁለት ቀናት የኢትዮጵያ ቡና ፕሮሞሽን ቀን ተብሎ በተሰየመበት መሰረት ተሳትፎ አድርጓል::

መርሃ ግብሩ በቻይና በተለይም በወጣቱ ዘንድ የጨመረ የመጣውን የቡና ፍላጎት ተከትሎ የቡና አብቃይ ሀገራትን የቡና ዓይነት ለማስተዋወቅ ታልሞ የተዘጋጀ ነው ተብሏል።

በዚህም በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲን ጨምሮ የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች መሳተፋቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

እንዲሁም የኢትዮጵያን ቡና ለቻይና ቡና ወዳዶች፣ ለካፌ ባለቤቶችና በቡና ገቢ ንግድ ላይ ለተሰማሩ ድርጅቶች የማስተዋውቅና በፓናል ውይይት ላይ በመሳተፍ ለተነሱ ጉዳዮች ማብራሪያ ተሰጥቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.