በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ100 ቀናት እቅድ አተገባበር ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ100 ቀናት እቅድ አተገባበር ላይ በሆሳዕና ከተማ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
በውይይት መድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው እና የዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
መድረኩ በጸጥታ ፣ በጤና፣ በግብርና፣ በትምህርት እና በገቢ አሰባሰብ ላይ ያተኮረ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡