Fana: At a Speed of Life!

ድርቅ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የሰብዓዊ ድጋፍ ስራዎቸ እየተከናወኑ ነው – ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የሰብዓዊ ድጋፍ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የፌዴራል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማሪያም ገለጹ።

ኮሚሽነሩ በተለይም በአማራና ትግራይ ክልሎች የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህ ሳምንት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው 7 ነጥብ 2 ሚሊየን ዜጎች በአይነትና በገንዘብ በአጠቃላይ ከ4 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

የአይነት ድጋፎቹ የህፃናት አልሚ ምግቦች እና የእለት ደራሽ ምግቦች መሆናቸውን የገለፁት ኮሚሽነሩ÷ ድጋፉ ቅድሚያ ለሚያስፈልጋቸው ተጎጂዎች ትኩረት መስጠቱን አብራርተዋል፡፡

የድርቅ አደጋ ምላሽ የህብረተሰቡንና በየደረጃው ያሉ የመንግስት መዋቅሮችን ርብርብ የሚፈልግ በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአፈወርቅ እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.