የአደባባይ በዓላትን ለቱሪዝም ማበልጸጊያነት መጠቀም እንደሚገባ ተመለከተ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበሩ የአደባባይ በዓላትን ለቱሪስት መዳረሻነት በመጠቀም ቱሪዝሙን ማሳደግ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
ዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ደረጃ እየተካሄደ የነበረው የኢሬቻ የፓናል ውይይት ዛሬ ተጠናቋል፡፡
የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ÷የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ዕሴቱን ጠብቆ፣ ሰላምና መተሳሰብ ነግሶበት፣ ፍቅርና መረዳዳት ተመክሮበት ይከበራል።
ኢሬቻ የፍቅርና የሰላም እሴት ማሳያ፣ ፈጣሪ የሚመሰገንበት ታላቅ የምስጋና በዓል እና የሰው ልጆች በእኩልነት የሚያከብሩት የሰላምና የፍቅር በዓል መሆኑንም ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ከንቲባ ጃንጥራር አባይ በበኩላቸው ÷የኢሬቻ በዓል ክረምቱ አልፎ ብራ ሲሆን ተፈጥሮን የፈጠረ ፈጣሪ የሚመሰገንበት የምስጋና በዓል በመሆኑ እሴቱን ጠብቆ በመዲናዋ ይከበራል ብለዋል፡፡
የከተማዋ ነዋሪዎች በሁሉም የከተማዋ መግቢያና መውጫ በሮች እንግዶችን በተለመደ ኢትዮጵያዊ ባህል እንዲቀበሉ ጥሪ ማቅረባቸውንም የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡