Fana: At a Speed of Life!

ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለን ግንኙነት ከፖለቲካዊ ወደ ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንዲያድግ በትኩረት ይሰራል – ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላት ግንኙነት ከፖለቲከዊ ወደ ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንዲያድግ በትኩረት ይሰራል ሲሉ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንቷ ባለፈው ዓመት በዲፕሎማሲያዊ ዘርፍ የተገኘውን ስኬት የሀገሪቱን ውጭ ጉዳይ ፖሊስ በመጠበቅ አፈጻጸሙ ወደ ላቀ ደረጃ እንዲያድግ ይሰራል ብለዋል፡፡

በዚህ መሰረትም ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላት ግንኙነት ከፖለቲከዊ ወደ ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንዲያድግ በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የሚደረጉ ድርድሮች የሀገራችንን በተፈጥሮ ሃብቷ የመልማት መብት እንዲሁም የተፋሰሱን የመልማት እድል በማይነፍግ መልኩ ይከናወናል ሲሉ አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ድንበር ከምትጋራቸው ሀገራት ጋር ያልተጠናቀቁ የድንበር ጉዳዮችን በዓለም አቀፉ ሕግ መሰረት ምላሽ እንዲያገኙ የበሰለ ዲፕሎማሲያዊ ስራዎች ይከናወናሉ ብለዋል፡፡

የድንበር ጉዳዮች ብሔራዊ ጥቅሞቻችን እና ዘላቂ ጎረቤታዊ ወዳጅነትን ታሳቢ በማድረግ ምላሽ እንዲያገኙም በትብብር እንደሚሰራ አስገንዝበዋል፡፡

በአጠቃላይ የውጭ ግንኙነታችን ወዳጅ የሚያበዛ፣ ጠላትን የሚቀንስ እንዲሁም የልማት አጋሮችን የሚያቅፍ እንዲሆን ይሰራል ነው ያሉት፡፡

 

በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.