የዳያስፖራውን ዐቅም ለመጠቀም በትኩረት ይሠራል – አገልግሎቱ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣይ ለዳያስፖራ ተሳትፎ ምቹ ሁኔታዎችን በማስፋት የዳያስፖራውን ማኅበረሰብ ዐቅም ለመጠቀም በትኩረት እንደሚሠራ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ገለጸ፡፡
በተያዘው በጀት ዓመት የዳያስፖራ ማኅበረሰብ ልማትና ተሳትፎ ሥራዎችን አጠናክሮ መቀጠል በሚቻልበት አግባብ ላይ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት በሚሲዮኖች ከሚሠሩ የዳያስፖራ ዲፕሎማቶች ጋር መክሯል፡፡
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እንድሪስ (ዶ/ር) በውይይቱ ላይ እንዳሉት÷ የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከዳያስፖራ መደበኛ ተሳትፎ አንጻር በርካታ ውጤቶች የታዩበት ነው፡፡
ወቅታዊ ሁኔታዎችን ተሻጋሪ የዳያስፖራ ተሳትፎን ማረጋገጥ እንዲሁም በአገልግሎቱ የተዘጋጁ ፓኬጆችና ፕሮጀክቶችን በመተግበር የዳያስፖራውን የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ማሳደግ የቀጣይ ትኩረት መሆናቸውን ነው ያብራሩት፡፡