Fana: At a Speed of Life!

አቶ ዓለምአንተ አግደው ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍትሕ ሚኒስትር ዴኤታ ዓለምአንተ አግደው በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ከሚገኙት የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኤሚ ኢ.ፖፕ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም÷ በኢትዮጵያ ያለውን የስደት አስተዳደር ሕጋዊ እና ተቋማዊ ማዕቀፎችን ሚኒስትር ዴኤታው አብራርተዋል፡፡

ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅትም በስደተኞች አስተዳደር፣ በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ እያበረከተ ስላለው አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡

በውይይታቸው ሚኒስትር ዴኤታው በኢትዮጵያ ያለውን የስደት አስተዳደር  እና ህጋዊ ማዕቀፉን  በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት በህገ ወጥ ሰዎች ዝውውር የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ሚና መጫዎቱን ጠቅሰው ለዚህም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኤሚ ኢ. ፖፕ በበኩላቸው ÷ የኢትዮጵያ መንግስት የተሻለ የስደት አስተዳደርን ለማስፈን እና ከስደት ጋር ተያይዞ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት አድንቀዋል፡፡

በተጨማሪም የዓለም ፍልሰተኞች ድርጅት ከኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ የብሔራዊ የነፃ የህግ ድጋፍ ስትራቴጂ ማፅደቋን ያደነቁት ዋና ዳይሬክተሯ÷ ነፃ የህግ ድጋፍ በመንግስት ተዋረድ ተግባራዊ እንዲሆን ድጋፍ እናደርጋለን ማለታቸውን የፍትህ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.