Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ በሕገ-ወጥ ንግድ በተሳተፉ 1 ሺህ የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሕገ-ወጥ ንግድ በተሳተፉ ከ1 ሺህ በላይ የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ሃላፊ አቶ ታሪኩ ኩመራ እንደገለጹት÷ መንግስት በክልሉ የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለመቀነስ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተቀናጀ የቁጥጥር ሥራ እያከናወነ ነው፡፡

በንግድ ሥርዓቱ ውስጥ የሚስተዋለውን ሕገ-ወጥ የደላሎች እንቅስቃሴና የንግድ ሰንሰለት ለመቆጣጠር የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን አብራርተዋል።

እስካሁን በተከናወኑ የቁጥጥር ሥራዎችም በሕገ-ወጥ ንግድ ሥራ በተሳተፉ ከ1 ሺህ በላይ የንግድ ድርጅቶች ላይ የተለያዩ እርምጃዎች እንደተወሰዱ መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.