Fana: At a Speed of Life!

እስራዔል የእግረኛ ጦር ማስፋፋቷን ተከትሎ በጋዛ የመገናኛ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋረጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራዔል የምድር ጦር ዘመቻዋን ማስፋፋቷን ተከትሎ በጋዛ የመገናኛ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ መቋረጡ ተሰምቷል፡፡

እስራዔል ወደ ጋዛ የእግረኛ ጦር ለማስገባት ያወጣችውን ዕቅድ ማራዘሟን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ቢያስታውቁም÷ በውሳኔው የእስራዔል የጦር ካቢኔ ስምምነት ላይ ባልደረሰበት ሁኔታ የእስራዔል የእግረኛ ጦር በጋዛ እንቅስቃሴውን ማስፋፋቱ ተገልጿል፡፡

ይህን ተከትሎም ምሽት በጋዛ የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት መቋረጡን በጋዛ የሚገኘው የሀገር ውስጥ የቴሌኮም አቅራቢ አስታውቋል፡፡

የእስራኤል ወታደሮች እና ታንኮች ወደ ጋዛ መግባታቸውን እና በሰሜን ጋዛ ከሃማስ ግጭት መፈጠሩን ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡

በፈረንጆቹ ጥቅምት 7 ሃማስ በከፈተው ጥቃት በተቀሰቀሰው ጦርነት እስራዔል በወሰደችው አፀፋ እስካሁን የ7 ሺህ 326 ፍልስጤማውያን ሕይወት ሲያልፍ 18 ሺህ 926 ቆስለዋል፡፡

በአንጻሩ ሃማስ ባደረሰው ጥቃት የ1 ሺህ 400 እስራዔላውያን ሕይወት አልፏል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.