አምባሳደር ፍጹም አረጋ በኦታዋ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ ቦርድ አባላት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ በኦታዋ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ ቦርድ አባላት ጋር ውይይት አደረጉ።
አምባሳደሩ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ከቦርድ አባላቱ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸው፣ አባላቱ በችግር ላይ የሚገኙ ዜጎችን ለመርዳት እያደረጉ ስላለው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።
አክለውም በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የጀመሩትን ስራ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ያላቸውን ተስፋ መግለጻቸውን የኢትዮጵያ የዳያስፖራ አገልግሎት መረጃ ያመላክታል፡፡