Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ 13 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሶስት ወራት 13 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ በሩብ ዓመቱ በባሕር ትራንስፖርት አገልግሎት 971 ሺህ 438 ቶን ገቢ ጭነት እና ከ200 ሺህ ቶን በላይ ወጪ ጭነት በባሕር ማጓጓዙ ተገልጿል፡፡

በጭነት አስተላላፊነት አገልግሎት በኩል 29 ሺህ 557 ኮንቴይነር እና 411 ተሽከርካሪዎችን በመልቲሞዳል ስርዓት ወደ ሀገር ውስጥ ወደቦችና የጉምሩክ ፈቃድ ያላቸው መጋዘኖች ማድረስ መቻሉም ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም 832 ሺህ 70 ቶን ገቢ ጭነት እና 83 ሺህ 662 ቶን ወጪ ጭነት በዩኒሞዳል የትራንስፖርት ስርዓት ማስተላለፍ መቻሉን የድርጅቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

በሩብ ዓመቱ በአጠቃላይ ለ104 ሺህ 659 ኮንቴይነሮች በወደብና ተርሚናሎች አገልግሎት መሰጠቱም ተጠቅሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.