Fana: At a Speed of Life!

ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ከጅቡቲ የመሰረተ ልማትና ኢኪዩፕመንት ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ከጅቡቲ የመሰረተ ልማትና ኢኪዩፕመንት ሚኒስትር ሃሰን ሁመድ ኢብራሂም ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም÷የሀገራቱን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ የልማትና የወዳጅነት የትብብር መስኮች ላይ መክረዋል፡፡

ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ኢትዮጵያና ጅቡቲ ዘመናትን የተሻገረ ጥልቅ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ገልጸዋል።

የሁለቱን ሀገራት ዜጎች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግም በመሰረተ ልማት ግንባታና ሌሎች ዘርፎች ለማስተሳሰር ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኗን አረጋግጠዋል።

ሃሰን ሁመድ ኢብራሂም በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያና ጅቡቲ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እንደመጣ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በቀጣይም የሁለቱን ሀገራት የወደብና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ትብብር በማስፋት የሀገራቱን ሕዝቦች ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንሰራለን ብለዋል።

በውይይቱ የጅቡቲ ወደብና ነፃ የንግድ ቀጣና ባለሥልጣን ሊቀ-መንበር አቦበከር ዑመር ሀዲ፣ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ዴንጌ ቦሩ፣ በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬና ሌሎች የሁለቱ ሀገራት የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.