Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት በሰሜን ዕዝና በፖሊስ አባላት ላይ የተፈፀመውን ጥቃት አሰቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በመከላከያ ሠራዊት ሰሜን እዝ እና በፌደራል ፖሊስ ሰሜን ዲቪዥን አመራር እና አባላት ላይ የተፈፀመውን ጥቃት አስበው ዋሉ፡፡

ክስተቱ የትም መቼም መደገም እንደሌለበት በሥነ- ሥርዓቱ ላይ የተገለጸ ሲሆን÷ መከላከያ ሠራዊትና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የኢትዮጵያ ኅልውና የመጨረሻ ምሽጎች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት መከላከያ ሠራዊትና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለኢትዮጵያ እየከፈሉ ያሉትን መሥዋዕትነት በማቃለል የሐሰት ቅስቀሳ የሚያሰራጩ አካላትም ከባለፈው ስህተት ተምረው ከእኩይ ተግባራቸው ሊታቀቡ ይገባል ተብሏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.