Fana: At a Speed of Life!

ለአፋር ክልል ጤና ቢሮ 15 ተሽከርካሪዎች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ለአፋር ክልል ጤና ቢሮ አምስት አምቡላንሶችን ጨምሮ የ15 ተሽከርካሪዎች ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉን በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተወካይ ዶክተር አቡበከር ካምፖ ለአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ አስረክበዋል፡፡

የተደረገው ድጋፍ በአፋር ክልል ያለውን የጤና ዘርፍ በተለይም ለተንቀሳቃሽ የጤና አገልግሎት (ሞባይል ሄልዝ ቲም) የሚውል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ዩኒሴፍ የዛሬውን ጨምሮ ላለፉት ሦስት ዓመታት በአንበጣ፣ በድርቅ እና በጦርነት ጊዜ ለክልሉ ላደረገው ድጋፍ አቶ አወል ምስጋና አቅርበዋል።

ዶክተር አቡበከር ካምፖ በበኩላቸው÷ ድጋፉ በትክክል ለሕዝቡ በተለይም እናቶችና ሕጻናት ሞት ቅነሳ ላይ ትኩረት እንዲያደርግ ታስቦ የተለገሰ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡

ተሽከርካሪዎቹ የተገዙት ከዩ ኤስ ኤይድ የሰብዓዊ ዕርዳታ ቢሮ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ መሆኑን የዩኒሴፍ ኢትዮጵያ መረጃ ያመላክታል፡፡

በዓሊ ሹምባሕሪ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.