Fana: At a Speed of Life!

መሪዎች ኢንቨስትመንትን ዋነኛ የኢኮኖሚ ዕድገት ሞተር አድርገው ሊጠቀሙበት ይገባል – የአፍሪካ ልማት ባንክ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መሪዎች ኢንቨስትመንት ማስፋፋትን ዋነኛ የአህጉሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት ሞተር አድርገው ሊጠቀሙበት እንደሚገባ የአፍሪካ ልማት ባንክ ገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከሞሮኮ ማራካሽ ከተካሄደው የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ፎረም ጎን ለጎን ቢግ ዊን ፊላንትሮፒ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ በጋራ ባዘጋጁት የከንቲባዎችና አጋር ድርጅቶች መድረክ ላይ ተገኝተዋል፡፡

የቢግ ዊን ፊላንትሮፒ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጄሚ ኩፐር በዚሁ ወቅት÷ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለሕፃናት መጫወቻና ለወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያ እንዲውሉ በመዲናዋ ከ12 ሺህ በላይ የመጫወቻ ሜዳዎችን ለመገንባት በቁርጠኛነት በመስራት ላይ እንደሚገኙም ጄሚ ኩፐር ጠቅሰዋል፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አኪንዋም አዴሲና በበኩላቸው÷ የከንቲባዎች ፎረም የአፍሪካን ዕድገትና ልማት ለማፋጠን በፋይናንስ ተቋማት፣ በከተሞችና በክልሎች መካከል አዲስ የትብብር በር መከፈቱን ገልፀዋል፡፡

በአፍሪካ ኢንቨስትመንት ፎረም ውስጥ ያሉ አጋሮችና ባለሀብቶች ኢንቨስትመንቶችን ለመደገፍ ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም መሪዎች ኢንቨስትመንት ማስፋፋትን ዋነኛ የአህጉሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት ሞተር አድርገው ሊጠቀሙ እንደሚገባ ጠቅሰዋል፡፡

በመድረኩ የአዲስ አበባ፣ ሌጎስ፣ ዳካር፣ አቢጃን፣ ኪጋሊ እና ናይሮቢን ጨምሮ የበርካታ የአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎች፣ አስተዳዳሪዎች እንዲሁም የመንግስትና የፋይናንስ፣ የልማት ተቋማት ተወካዮች መሳተፋቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.