Fana: At a Speed of Life!

በቻይና የሚደገፈው የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል ላቦራቶሪ በኢትዮጵያ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና የሚደገፈው የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል (አፍሪካ ሲዲሲ) ላቦራቶሪ በኢትዮጵያ ተከፍቷል፡፡

የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል (አፍሪካ ሲዲሲ) በቻይና የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለትን ከፍተኛ ላቦራቶሪ በኢትዮጵያ ዋና መሥሪያ ቤቱን ይፋ ያደረገ ሲሆን ይህም ለቻይና የጤና ዲፕሎማሲ ሌላ ምዕራፍ ፈጥሯል ተብሏል።

በፈረንጆቹ 1911 የማንቹሪያ ወረርሽኝን ለማጥፋት በረዱት በቻይና-ማሌዥያ የመድሃኒት ተመራማሪ ዶክተር ው ሊን ቴህ የተሰየመው ላቦራቶሪ በአፍሪካ የላቦራቶሪ ስርዓት ክፍተቶችን ለመፍታት ያለመ ነው።

በአራት-ደረጃ ስርዓት ውስጥ ሁለተኛ ከፍተኛ ደረጃ የተሰጠውን ሁለት ከፍተኛ የባዮሴፍቲ ደረጃ 3 ላቦራቶሪዎችን ያካተተ መሆኑም ተመላክቷል።

ድርጅቱ የስልጠና እና የጥራት ማረጋገጫ ማዕከል ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን የምርመራ ቴክኖሎጂዎችን እና መሳሪያዎችን የመገምገም እና የማረጋገጥ ድጋፍም ይሰጣል ተብሏል።

በተጨማሪም ምርምር እና ልማትን የመደገፍ እና ወረርሽኝን በማረጋገጥ ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተጠቁሟል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ ውስጥ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን እና የቁጥጥር መስፈርቶችን ባከበረ መልኩ በሀገር ውስጥ ቅድሚያ የሚሰጣቸው በሽታዎችን ለመመርመር እና ናሙናዎችን በትክክል ለማጓጓዝ ሙሉ በሙሉ የዳበረ እና ዘላቂ አቅም ያላቸው ላቦራቶሪዎች ከአምስት በመቶ በታች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአፍሪካ ሲዲሲ ዋና መስሪያ ቤት በ80 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ በቻይና መንግስት ተገንብቶ ለአፍሪካ ህዝብ በስጦታ መበርከቱ ተገልጿል።

ባለፈው አርብ በተካሄደው የርክክብ ሥነ-ሥርዓት ላይ የቻይና ሲዲሲ ዳይሬክተር ዶክተር ሼን ሆንግቢንግ እና የአፍሪካ ህብረት የቻይና ተልእኮ ኃላፊ ሁ ቻንግቹን ሁለቱ ሲዲሲዎች በምርመራ፣ ለወረርሽኞች ምላሽ በመስጠት እና በቅድመ ማስጠንቀቂያ በጋራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

በፈረንጆቹ ከ2017 ጀምሮ የቻይና ሲዲሲ የተላላፊ በሽታ ክትትል፣ የላቦራቶሪ ትስስር እና የመረጃ ስርዓቱን ለማጠናከር አምስት ባለሙያዎችን ወደ አፍሪካ አቻው መላኩን ቻይና ኢኮኖሚ ዘግቧል።12:24

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.