ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የንጽህና አጠባበቅ አጀንዳን ለማፋጠን ተስማሙ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት እና የዓለም ባንክ የውሃ፣ የአካባቢ እና የግል ንፅህና አጠባበቅ የ(ዋሽ) አጀንዳን ለማፋጠን በትብብር ለመስራት መስማማታቸው ተገለጸ፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር በምስራቅና ደቡብ አፍሪካ የ(ዋሽ) የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን የኢትዮጵያን የውሃ፣ የአካባቢ እና የግል ንፅህና አጠባበቅ የ(ዋሽ) አጀንዳ ስልቶች ላይ ምክክር አድርጓል።
በዓለም ባንክ የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ቪክቶሪያ ክዋክዋ እና በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የተመራው ውይይት ሁለቱም ወገኖች አሁን ባለው የውሃ ፖርትፎሊዮ ውስጥ ያሉ ተግባራትን ሂደት እንዲገመግሙ እድል መፍጠሩ ተመላክቷል።
የውይይቱ ግብም በ(ዋሽ) አመራር ጉባኤ ወቅት የተነሱ ሀሳቦችን በኢትዮጵያ ተጨባጭ ወደ ሆነ ተግባር ለመተርጎም ያለመ እንደነበር ተገልጿል።
ኢትዮጵያ የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር ውሃ ሀብቶችን በማከማቸትና በማስተዳደር በንጽህና አጠባበቅ አገልግሎት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እድገት ብታስመዘግብም አሁንም በሚሊየን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እነዚህን ወሳኝ አገልግሎቶች አያገኙም ተብሏል።
ይህም የተደራሽነት ችግር ድህነትን ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት ያደናቅፋል ነው የተባለው።
በተጨማሪም፣ መሠረታዊ የውኃ አቅርቦትና የንፅህና አጠባበቅ ፍላጎትን ለማሟላት የገንዘብ ፍላጎቱ እየጨመረ ሲሆን የሀገር ውስጥ የገንዘብ ድጋፍ ግን አሁንም ውስን መሆኑ ተገልጿል።
በቂ ያልሆነው የገንዘብ ድጋፍና በነባር ኢንቨስትመንቶች ላይ ያለው ብቃት ማነስን ጨምሮ የአሰራር ቅልጥፍና ፣ የውሃ ማፍሰስ እና በገጠር አካባቢዎች ያሉ አዳዲስ የውሃ ቦታዎች አለመሳካት ቀድሞውንም እጥረት ውስጥ ያለውን የህዝብ ሀብት እንደሚያባክኑት ነው የተመላከተው።
እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት ሁለቱም ወገኖች ሁለንተናዊ የአገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ አቋም መያዛቸው ተጠቅሷል።
በተለይም በዓለም ባንክ የሚደገፉ ፕሮጀክቶች የንፅህና አጠባበቅ አገልግሎት ተደራሽነትን በሚያሳድጉ፣ የአየር ንብረት አደጋዎችን የመቋቋም እና የንፅህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ዘላቂነት ለማሳደግ በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!