Fana: At a Speed of Life!

መንግስት ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱን ለመቀጠል መወሰኑን በደስታ ይቀበለዋል -አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) በኢትዮጵያ የሚያደርገውን የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ለመቀጠል ያሳለፈውን ውሳኔ በደስታ እንደሚቀበለው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮነን ተናገሩ፡፡

አቶ ደመቀ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳስታወቁት፥ መንግስት ሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ብቻ እንዲደርስ በቁርጠኝነት ይሰራል፡፡

መንግስት ባለፉት አምስት ወራት ከዩ ኤስ ኤ አይ ዲ እና ከሌሎች የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን አጋሮች ጋር በመተባበር የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱን ለማሳደግ ያለውን ቁርጠኝነት አሳይቷል ብለዋል።

የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱን በማሻሻል እርዳታ ለሚያስፈልጋቸውን ወገኖችን የመርዳት እና መልሶ የማቋቋም ሂደቱን ማፋጠን እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

የአሜሪካ መንግስት በዩ ኤስ ኤ አይ ዲ በኩል የሚደረገው የሰብዓዊ ድጋፍ ለትክክለኛ ተጎጂዎች አልደረሰም በሚል ለአምስት ወራት ያህል በኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አቋርጦ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.