በአራቱም የጎጃም ዞኖች የሰላም ሁኔታ ከፍተኛ መሻሻሎች እያሳየ መሆኑ ተመላከተ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በአራቱም የጎጃም ዞኖች እና ወረዳዎች ያለው የሰላም ሁኔታ ከፍተኛ መሻሻሎች እያሳየ መሆኑን ኮማንድ ፖስቱ አረጋገጠ።
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት የዕቅድ አፈጻጸሙን በደብረማርቆስ ከተማ በገመገመበት ዕለት እንደተገለጸው ፥ በጎጃም ባሉ ሁሉም ዞኖችና ከተሞች በተሰራው ህግ የማስከበር ስራ ለውጥ ታይቷል ።
በአማራ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተደድር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው እንዲሁም የምስራቅ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሐመድ ተሰማ እንደተናገሩት ፥ ሠራዊቱ በተሰማራባቸው ሁሉም አካባቢዎች የመንግስት መዋቅር መልሶ እየተደራጀ ነው።
ፖሊስ ፣ ሚሊሻ እና ሌሎች አካላት ከመከላከያ ጋር ተሰልፈው ግዳጅ እየተወጡ እንደሚገኙ መገለጹን ከመከላከያ ሠራዊት የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በተጨማሪም የጽንፈኛው ቡድንም ከህዝብ እየተነጠለ መጥቷል ፤ የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማትም ስራ ጀምረዋል ተብሏል ።
የውይይቱ ተሳታፊዎች ሰላሙ ቀጣይ እንዲሆን የፖለቲካ አመራሩ የህዝብ ግንኘነት ስራ በማጠናከር ፣ የፖሊስ ፣ የሰላም ማስከበር እና የሚሊሺያ አባላትን በማደራጀት ፣ የህዝብ አገልግሎትን በተደራጀ መንገድ በመምራት ከሠራዊቱ ጎን በመሆን የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ማረጋገጣቸውም ተገልጿል ።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!