Fana: At a Speed of Life!

ሬድ ፕላስ የደን ልማት ኢንቨስትመንት ፕሮግራም ሁለተኛ ምዕራፍ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ኅዳር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘ሬድ ፕላስ’ የተባለ የደን ልማት ኢንቨስትመንት ፕሮግራም ሁለተኛው ምዕራፍ መጀመሩን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ ÷ ደን የምግብ፣ የእንጨት፣ የእንስሳት መኖ እና መድኃኒት ሊሆኑ የሚችሉ ዕጽዋት ለሰው ልጆች ያቀርባል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ በብዝሃ ህይወት የበለፀጉ የደን ስነ-ምህዳሮች የጎርፍ አደጋን በመከላከል፣ የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ፣ ግድቦች በደለል እንዳይሞሉ ማበድረግ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታን እያበረከተ ይገኛል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የደን ዘርፉን ለመለወጥ የሚያስችሉ አዳዲስ ፈጠራዎችን እየተገበረች መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ÷ በዚህም በብዝሀ ሕይወት የበለፀጉ ደኖችን መጠበቅ እና የተራቆቱ መሬቶችን ወደ ነበሩበት መመለስ መቻሉን አስገንዝበዋል፡፡

የተለያዩ የዕጽዋትና የዱር እንስሳት መገኛ የሆነችው ኢትዮጵያ በብዝሃ ህይወት ከሚታወቁ አምስት ሀገራት አንዷ ናት መባሉን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሬድ ፕላስ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት የካርበን ልቀትን ለመቀነስ እና የግሪን ሃውስ ጋዞች ለማስወገድ የሚያድርጉትን ጥረት በፋይናንስ እና በቴክኒክ የሚደግፍ ማዕቀፍ ነው፡፡

በተለይም የደን ልማት ላይ በመስራት የደን መመናመን ችግሮችን ለመከላከል የሚሰራ ፕሮጀክት ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.