Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የወንጀል መከላከል ስትራቴጂ ማስፈጸሚያ ሰነድ ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2016 (ኤ ፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የወንጀል መከላከል ስትራቴጂ ማስፈጸሚያ ሰነድ መዘጋጀቱን ፍትሕ ሚኒስቴር አስታወቀ።
 
የፍትሕ ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የወንጀል መከላከል ስትራቴጂ ማስፈጸሚያ ሰነድ ላይ ከሚመለከታቸው የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ውይይት አካሂዷል፡፡
 
ሀገር አቀፍ የተቀናጀ ወንጀል መከላከል ስትራቴጂ በሀገርና ህዝብ ሰላም፣ ደህንነትና ጥቅም ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በመከላከልና በመቀነስ የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ለማስጠበቅ በ2012 ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት የጸደቀ ነው።
 
ስትራቴጂው የሽብር፣ በመሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈጸሙ፣ ከባድ የኢኮኖሚና ከገንዘብ ጋር ተያይዘው የሚፈጸሙ፣ ግድያና ውንብድና፣ በሴቶች እና ህፃናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡
 
ከዚህ በተጨማሪም የሙስና፣ በሰው የመነገድና ስደተኞችን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር፣ የመንገድ ትራፊክ ህግ ጥሰት እና በዜጎች ሰላምና ደህንነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በቅንጅት ለመከላከል የሚያስችል ነው ተብሏል።
 
የፍትሕ ሚኒስትር ዴኤታ ዓለምአንተ አግደው ወንጀል የዜጎችን መሰረታዊ ህይወት በማናጋት የሀገርን ህልውና የሚፈታተን ማህበራዊ ተግዳሮት ነው ብለዋል።
 
ወንጀልን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ባይቻልም አስቀድሞ በመከላከል የሚያደርሰውን ጉዳት መቀነስ እንደሚቻል መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
 
ስትራቴጂው በተለያዩ ምክንያቶች ተግባራዊ ሳይሆን የቆየ መሆኑን ጠቁመው፥ አሁን ላይ ህብረተሰቡን ያሳተፈ ትብብር በመፍጠር ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል የማስፈፀሚያ ሰነድ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.