Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ እና በኮሪያ መካካል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር ለማጠናከር ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2016 (ኤ ፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው ከኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) ፕሬዚዳንት ካንግ ዎን ሳም ጋር በኢትዮጵያ እና በኮሪያ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።
 
በውይይታቸው በኢትዮጵያ የማምረቻ አቅምን ማሳደግ፣ የጤና አጠባበቅ አገልግሎትን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽን ማሳደግ፣ የጥቃት ተጋላጭነትን የመቋቋም ችሎታን እና ማህበራዊ ትስስርን በስርዓተ-ፆታ ተኮር አቀራረብ ማጎልበት እና የተፋሰስ ልማትን ያጠቃለለ የ(ኮይካ) የወደፊት የትብብር መስኮች ላይ መክረዋል።
 
ኮይካ በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የልማት አጋር ሲሆን ድጋፉን ካለፉት ጊዜያት በተሻለ በ40 በመቶ ለማሳደግ ቃል መግባቱም ተመላክቷል።
 
የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው (ኮይካ) በኢትዮጵያ እያደረገ ላለው ወደ 294 ሚሊየን ዶላር የሚደርስ የልማት ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
 
በፈረንጆቹ 2023 (ኮይካ) 30 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ በጀት መመደቡን በማንሳትም ድጋፉ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ36 በመቶ ከፍ ያለ መሆኑን መግለፃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
ይህ አጋርነት ለኢትዮጵያ መልካም ዕድገት ሲሆን በቀጣይ አመታትም የሁለቱን ወገኖች ትብብር እንደሚያጠናክር ተስፋ ተጥሎበታል።
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.