ህብረተሰቡ በጋራ ለሰላም ሊሰራ እንደሚገባ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ህብረተሰቡ በጋራ ለሰላም ሊሰራ ይገባል ሲሉ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
ጎንደር ከተማን ወደ ተሟላ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለመመለስ ያለመ ውይይት መካሄድ ጀምሯል።
ውይይቱ በጎንደር ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ሁሉም ክፍለ ከተሞች በ95 ቀጠናዎች እየተካሄደ ነው።
የውይይት ተሳታፊዎች በጋራ ሆነን የራሳችንን ሰላም ማስጠበቅ ይገባናል ማለታቸውን ከከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ህብረተሰቡ ሰላምን ይፈልጋል ፤ ሰላምን ደግሞ ለማምጣት መነጋገር ያስፈልጋል ያሉት ነዋሪዎቹ፥ የአማራ ክልል የህዝብ ጥያቄዎችን መንግስት ፈጥኖ ምላሽ መስጠት ከቻለ ህብረተሰቡ እና መንግስት እጅና ጓንት ሆኖ መስራት ይቻላል ብለዋል፡፡
ሁሉም ሰው በሰላም መኖር ይፈልጋል፤ አመራሮች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ ህብረተሰቡ በጋራ ለሰላም ሊሰሩ እንዲገባም አንስተዋል።
መንግስት ደግሞ ህብረተሰቡ ለሚጠይቃቸው ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ይገባዋልም ነው ያሉት።
በውይቱ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት እየተሳተፉ ይገኛል፡፡