Fana: At a Speed of Life!

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሀገርን ወደ ከፍታ ያሻግራል – በለጠ ሞላ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰው ሰራሽ አስተውሎት በትኩረት ከተሰራበት ሀገርን ወደ ከፍታ ያሻግራል ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ሚኒስትሩን ጨምሮ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ በኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ኢ/ር) አማካኝነት ስለ ኢንስቲትዩቱ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ማብራሪያ ቀርቦላቸዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ በገለጻቸው፤ ኢንስቲትዩቱ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር ሊሰራባቸው የሚችሉ በርካታ የቴክኖሎጂ አማራጮች መኖራቸውን አመላክተዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ኢንስቲትዩቱ በጤና፣ በግብርና፣ በፍትሕ፣ በትምህርት እና በአገልግሎት ዘርፉ ውጤታማ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ በትኩረት ከተሰራበት ሀገርን ወደ ከፍታ ያሻግራል ያሉት ሚኒስትሩ÷ በቀጣይ ሁለቱ ተቋማቱ በልዩ ልዩ መስኮች ተቀራርበው በትብብር እንደሚሰሩ አመላክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.