Fana: At a Speed of Life!

የተቋም እድገት የሚለካው የመንግስትን ፖሊሲ ተግባራዊ በማድረግ ነው – ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተቋም እድገት የሚለካው ህግና ስርዓትን ተከትሎ የመንግስትን ፖሊሲ ተግባራዊ ማድረግ ሲችል እንደሆነ የኢፌዲሪ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ተናገሩ፡፡

የአየር ኃይል ፋይናንስ ስራ አመራር በፋይናንስ ግዢ በንብረት አስተዳደር እንዲሁም በእቅድና ሪፖርት ዝግጅት ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለተቋሙ ባለድርሻ አካላት ሰጥቷል።

በመድረኩ የተገኙት የአየር ሀይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ÷ የአንድ ተቋም እድገት በዋነኝነት የሚለካው መንግስት ባወጣቸው ህግና ስርዓት በመከተል ስራዎችን ማከናወን ሲችል እንደሆነ አስገንዝቧል።

በተለይም በፋይናንስና ግዢ በንብረት አስተዳደር እንዲሁም በእቅድና ሪፖርት ላይ የሚሰሩ ሙያተኞችና አመራሮች ሙያዊ አቅማቸውን ይበልጥ በማጎልበት ለተቋማዊ የለውጥ ጉዞ ስኬት የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

በኢፌዴሪ አየር ኃይል የፋይናንስ ስራ አመራር ዳይሬክተር ኮሎኔል በሻ ደገፋ÷ ስልጠናው በአየር ሀይል የፋይናንስ ዘርፍ  ለተያዘው ራዕይና ተልዕኮ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ማለታቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.