Fana: At a Speed of Life!

የአብሮነት ቀን በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል ዛሬ ህዳር 27 ቀን 2016 ዓ.ም የአብሮነት ቀን በሚል ስያሜ በልዩ ልዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው።

በመርሐ ግብሩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች አብሮነት እና ህብረ ብሔራዊነትን የሚያጎሉ ባህላዊ እሴታቸውን ለታዳሚዎች እያቀረቡ ይገኛሉ።

በተጨማሪም ባህላዊ ዜማዎችን እና ጭፈራዎችን በማቅረብ አንድነት በማሳያት የባህል መጋራት መርሐ ግብር እያካሄዱ ነው።

በጅግጅጋ የሚከበረው 18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል ”ብዝሃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ሁነቶች መከበሩ ቀጥሏል። በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.