Fana: At a Speed of Life!

በፍራንኮ ቫሉታ ከ6 ሚሊየን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ወደ ሀገር ገብቷል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምርቶች በፍራንኮ ቫሉታ እንዲገቡ በተዘረጋው ስርዓት ከ6 ሚሊየን ሊትር በላይ የፓልም ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱ ተገለጸ፡፡

የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት በ2016 በጀት ዓመት አራት ወራት ውስጥ ምግብ ዘይቱ በፍራንኮ ቫሉታ ስርዓት ወደ ሀገር መግባቱን የገለጸው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ነው፡፡

መንግስት ቀረጥና ታክስን በመተው በፍራንኮ ቫሉታ ለህብረተሰቡ ከውጭ እንዲገቡ ከፈቀዳቸው ምርቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የፓልም የምግብ ዘይት እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡

ይህም የዘይት ምርት እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2016 ባለው የበጀት ዓመቱ አራት ወራት ውስጥ 6 ሚሊየን 43 ሺህ 526 ነጥብ 69 ሊትር ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ ለገበያ ቀርቧልም ነው የተባለው፡፡

በተመሳሳይ መልኩ 2 ሚሊየን 377 ሺህ 727 ነጥብ 94 ኩንታል ስኳር እና 1 ሚሊየን 801 ሺህ 380 ነጥብ78 ኩንታል ሩዝ ወደ ሀገር ውስጥ ገበያ ገብቷል፡፡

እነዚህ ምርቶች ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ በመደረጉ በአቅርቦቱ ላይ ያለውን ክፍተት ለመሙላት ማስቻሉን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ አመላክቷል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.