ለሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ውጤታማነት የምክክሩ አማካሪ ኮሚቴ ሚና የጎላ መሆኑ ተጠቆመ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገራዊ ምክክሩ ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆንና የሚደረስባቸው መግባባቶች በተሟላ መልኩ እንዲፈፀሙ የሀገራዊ ምክክሩ አማካሪ ኮሚቴ ገንቢ ሚና መጫወት እንደሚገባው ኮሚሽኑ አስገነዘበ።
የቀጣይ የአማካሪ ኮሚቴ ሂደትና ሚና ላይ ያተኮረ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አማካሪ ኮሚቴ መድረክ መካሄድ ጀምሯል ።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት ÷ ሀገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ለሚታዩ የሀሳብ ልዩነቶችና መሰረታዊ ምክንያቶች ጥልቅ ምክክር እንዲደረግበት እየተሰራ ነው።
በዚህም በሀገር ደረጃ መግባባት በመፍጠር ሀገርን የማሻገር ተልዕኮ እንዲሳካ እንዲሁም የምክክር ሂደቱ አካታችና አሳታፊ እንዲሆን ኮሚሽኑ በትኩረት እየሰራ መሆኑን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የምክክር ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆንና የሚደረስባቸው መግባባቶች በተሟላ ሁኔታ እንዲፈፀሙ አማካሪ ኮሚቴ አባላት ተሰይመው እየሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል።
በዚህም የኮሚሽኑ የእስከ አሁኑ ሂደት ላይ አማካሪ ኮሚቴው የሰራቸውን ክንውኖችና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ ለመምከር የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ኮሚሽነር መላኩ ገልጸዋል ።
በተለይ በምክክር ሂደቱ ውጤታማነትና ሂደቱ ላይ ማነቆ ሊሆኑ የሚችሉ ተግዳሮቶች የሚፈቱባቸውን መንገዶች በማመላከት የአማካሪ ኮሚቴው ሚና ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል ።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!