የአፋር ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ምክር ቤት 6ኛ የምርጫ ዘመን 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባዔ የተለያዩ ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቅቋል።
በርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ አቅራቢነት በምክር ቤቱ ሹመታቸው ከፀደቀላቸው መካከል ቀደም ሲል በሥራና ክኅሎት ቢሮ በኃላፊነት ተመድበው ይሠሩ የነበሩት አቶ ኢለማ አቡበከር ይገኙበታል።
በተጨማሪም የአራት ዞኖች አስተዳዳሪዎችን ሹመት ምክር ቤቱ አጽድቋል፡፡
በዚህም መሰረት÷ አቶ አሊ ማቴ የኸሪ ረሱ ዞን አስተዳዳሪ፣ አቶ ማቴ ሐመድ የማሂ ራሱ ዞን አስተዳዳሪ፣ አቶ መሐመድ አሊ የቂልበት ራሱ ዞን አስተዳዳሪ፣ አቶ አብዱ ሐሰን አውሲ ራሱ ዞን አስተዳዳሪ በመሆን እንዲሰሩ ሹመታቸው መጽደቁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
እንዲሁም ምክር ቤቱ የአፋር መገናኛ ብዙኃንን የቦርድ አመራር አባላት የመረጠ ሲሆን÷ በዚሁ መሠረት አቶ መሐመድ ዓሊ የቦርዱ ሰብሳቢ፣ አቶ መሐመድ ቦዳያ አባል፣ ወ/ሮ ኤይሻ ያሲን አባል፣ አቶ መሐመድ አህመድ አባል፣ አቶ ገዶ ሐመሎ አባል፣ አቶ ሐሰን ዳውድ አባል እና አቶ ማህሙዳ መሐመድ አባል ሆነው እንዲሠሩ ጸድቋል፡፡