የሰላምን ጥሪ ለተቀበሉ ኃይሎች በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ስልጠና መሰጠት ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ አካባቢ መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ለተቀበሉ ኃይሎች በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል፡፡
የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ ተክለየስ በለጠ የሰላም ጥሪውን በመቀበል ስልጠናውን ለመውሰድ ለተዘጋጁ አካላት አስፈላጊ የስልጠና ሠነዶች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡
የአማራ ክልል ፕላን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አለባቸው ገነቴ በበኩላቸው÷ በክልሉ በሚገኙ ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎች ተመሰሳይ ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
ሰልጣኞችም በንቃት እንዲሳተፉ ጠይቀዋል፡፡
ሀገራዊና አካባቢያዊ ችግሮችን በኃይል ሳይሆን በሰላም ብቻ መፍታት እንደሚገባም የሐይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች መክረዋል፡፡
ዛሬ የተጀመረው ስልጠናም ለ10 ቀናት እንደሚቆይ ታቀውቋል፡፡
የአማራ ክልልን የመልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ከመፍታት ይልቅ ነፍጥ በማንገብ ከጸረ-ሰላም ኃይሎች ጋር ሲንቀሳቀሱ ለነበሩ አካላት ነው ስልጠናው እተሠጠ የሚገኘው፡፡
በታለ ማሞ