7 አባላት ያሉት የ“ሿሿ” ወንጀል ቡድን በቁጥጥር ሥር ዋለ
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ አካባቢዎች በተሽከርካሪ በመንቀሳቀስ በተለምዶ “ሿሿ” የተባለውን የስርቆት ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ ሰባት አባላት ያሉት የወንጀል ቡድን በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡
በቡድኑ አባላት ላይም ምርመራ እየተጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፍላሚንጎ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ከተጠርጣሪዎቹ ጋር እጅከፍንጅ የተያዙ ንብረቶች መኖራቸውን የገለጸው ፖሊስ÷ ወንጀል የተፈፀመበት ግለሰብ ደንበል አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቀርቦ ተጠርጣሪዎቹን መለየት እና ከተያዙትንብረቶች መካከል የራሱን መምረጥ እንደሚችል አስታውቋል፡፡