ዓየር መንገዱ ለ2ኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ከ15 እስከ 20 በመቶ ቅናሽ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ በውጭ የሚኖሩ ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት እንዲመጡ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ ለሚመጡ በአውሮፕላን ትኬትና በስካይላይት ሆቴል ላይ ከ15 እስከ 20 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
በተጨማሪም በኢ ቲ ሆሊደይስ አማካኝነት ለእንግዶች የሚሆን የጉብኝት መርሐ-ግብር በቅናሽ ዋጋ ማዘጋጀቱን ነው ዓየር መመንገዱ ያስታወቀው፡፡
በተጨማሪም አዲስ አበባን ለሚጎበኙ ከ100 በላይ እንግዶች የነፃ ፓኬጅ ማዘጋጀቱን ገልጿል፡፡
የዓየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ ለማ ያዴቻ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ ጥሪውን ተከትሎ የሚመጡ በርካታ እንግዶች የቅናሹ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በታሪኩ ወ/ሰንበት፣ መሳፍንት እያዩ እና ሜሮን ፈለቀ