Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከአለም ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ሀገራት ዳይሬክተር ከሆኑት ኡስማኔ ዲዮን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ርእሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ከዳይሬክተሩ እና ልዑካቸው ጋር በኦሮሚያ ክልል ስላለው አጠቃላይ ሁኔታና በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም የኦሮሚያ ክልል መንግስት አቅዶ ተግባራዊ እያደረገው ያለው የአስር ዓመት የልማት እቅድና እንዲሁም አጠቃላይ የክልሉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ስራዎች በተመለከተ ሰፊ ምክክር ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡

በቀጣይም የኦሮሚያ ክልል መንግስት በሚያከናውናቸውን የልማት ስራዎች ዙሪያ በትብብር ለመስራት ከስምምነት መድረሳቸውንም አመላክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.