ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከክልሎችና ከተማ አስተዳደር ከተወጣጡ ተወካዮች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተለያዩ ክልሎችና ከተማ አስተዳደር ከተወጣጡ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ፥ ዛሬ ሰፊ መጠነ ርዕይ ባላቸው ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከሶማሌ፣ አፋር፣ ሀረሪ፣ ጋምቤላና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች እንዲሁም ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከተወጣጡ ተወካዮች ጋር መምከራቸውን ገልጸዋል፡፡
‘’ውይይታችን በልማት፣ ሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ያጠነጠነ ነበር’’ ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡