በሰው ሠራሽ አስተውሎት አሥተዳደር ላይ ያተኮረ መድረክ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፋዊ የሰው ሠራሽ አስተውሎት አሥተዳደር ሥርዓት ጅምሮች እና የኢትዮጵያ ትልም በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ምክክር እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴዔታ ይሽሩን ዓለማየሁ (ዶ/ር)፣ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጽ/ቤት ኃላፊ አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን ተገኝተዋል።
አቶ ጃፋር በድሩ በዚሁ ወቅት ኢንስቲትዩቱ ለኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲመዳበር የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ገልፀው÷ በዚህም በዘርፉ ችግር ፈቺ የሆኑ ሐሳቦችን እያመነጨ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የመድረኩ ዓላማም የሰው ሠራሽ አስተውሎት በውጭ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ ተልዕኮ ላይ ያለውን ጠቀሜታ እና ተጽዕኖ ማስገንዘብ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የሰው ሠራሽ አስተውሎት በየጊዜው ማደግ ስጋት ይዞ መምጣቱንም ጠቅሰው፥ ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ በዘርፉ በንቃት መሳተፍ እንደሚገባት አስገንዝበዋል፡፡