የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በጎንደር ከተማ የልማት እንቅስቃሴዎችን እየጎበኙ ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደና የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አይሻ መሃመድን (ኢ/ር) ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በጎንደር ከተማ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ሃላፊ አቶ አበበ ላቀው እንደተናገሩት÷ በከተማ አስተዳደሩ ሰላምን ከማስከበር ባለፈ የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የልማት ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛሉ።
በከተማው የህዝብን የልማት ጥያቄ ለመመለስ በ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በጀት የተለያዩ የግንባታ ፕሮጀክቶች በመካሄድ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በፌደራል መንግስት እየተገነባ የሚገኘው የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውሃ ግድብ የስራ እንቅስቃሴ የጉብኝቱ አካል መሆኑ ተመልክቷል።
በተጨማሪ በከተማው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴና የግል ባለሃብቶች የስራ እንቅስቃሴዎች እንደሚጎበኙም ኢዜአ ዘግቧል፡፡