ኮሚሽኑ በባሕር ዳር ክላስተር ሲያካሂድ የቆየው የተባባሪ አካላት ስልጠና ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በባሕርዳር ክላስተር ሥር ከሚገኙ ወረዳዎች ለመጡ ተባባሪ አካላት ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና አጠናቅቋል፡፡
በስልጠናው ከምስራቅ ጎጃም፣ ከምዕራብ ጎጃም፣ ከሰሜን ጎጃም እና ከአዊ ዞኖች እንዲሁም ከባሕርዳርና ደብረ ማርቆስ ከተሞች የመጡ ከ250 በላይ ተባባሪ አካላት ተሳትፈዋል፡፡
በስልጠናው ላይ ኮሚሽኑ እስካሁን በ10 ክልሎችና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች ያከናወናቸውን እና በቀጣይ ስለሚያከናወኑ ተግባራት ማብራሪያ ቀርቧል፡፡
በተጨማሪም ተባባሪ አካላት ስለሚኖራቸው ተግባርና ሃላፊነት በኮሚሽኑ ኮሚሽነሮችና በዩኒቨርሲቲ መምህራን ገለጻ መደረጉን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡