Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በ2017 በጀት ጣሪያ ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ አስቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በ3ኛ ዓመት 13ኛ መደበኛ ስብሰባው የመካከለኛ ዘመን የ2017 በጀት ጣሪያ ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ አስቀምጧል።

ካቢኔው ዛሬ ባደረገው ከ2007 እስከ 2019 በጀት ዓመት የመካከለኛ ዘመን የወጪ ማዕቀፍ ውይይት መሰረት የ2017 በጀት ዓመት ከተለያዩ የገቢ አርዕስቶች 230 ነጥብ 39 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱ ተገልጿል።

የበጀት ድልድሉም ከጠቅላላ በጀት ውስጥ 61 መቶ ለካፒታል ወጪ ሆኖ በጀቱም በዋናነት በቅርቡ በከተማ አስተዳደሩ የትራንስፎርሜቲቭ ፕላን ዝግጀት ለተያዙ ቁልፍና እድገት ተኮር ዘርፎች የበጀት ድልድሉ የትኩረት አቅጣጯ መሆን አንዳለበት ካቢኔው መወያየቱ ተጠቁሟል።

በመጨረሻም አዲስ አበባ በገቢ ግብር በጀቷን የምታስተዳድር ከተማ እንደ መሆኗ መጠን የገቢ አቅሟን አሟጦ መሰበሰብ የሚገባ መሆኑ አጽንኦት ተሰጥቷል፡፡

የገቢ አሰባሰብ ስርዓት ላይ ትኩረት ሰጥተው ተቋማት መስራት የሚችሉበት ቀጣይ አቅጣጫም በትኩረት ድጋፍ እና ክትትል እንደሚደረግበት ውሳኔ ማሳለፉንም የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.