Fana: At a Speed of Life!

966 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 966 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከተመላሾቹ ውስጥ 641 ወንዶች፣ 321 ሴቶችና 4 ጨቅላ ህፃናት መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን ወደ ሃገር የመመለስ ጥረት እስካሁን ከ38 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል ነው የተባለው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.