በሀዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀዋሳ ከተማ ‘የኮሪደር ልማት ለላቀ ከተማችን ውበት” በሚል መሪ ቃል የከተማዋ ኮሪደር ልማት ስራ ተጀምሯል፡፡
በኮሪደር ልማት ስራው በከተማዋ በ1 ቢሊየን 64 ሚሊዮን ብር 11 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የከተማዋ የኮሪደር ስራ ይከናወናል ተብሏል፡፡
በተጨማሪም ከዳቶ እና ጨፌ ሰፈሮች ወጣ ብሎ የሚገኘውን የ34 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር መንገድ 2 ቢሊየን 64 ሚሊዮን ብር ወጭ በማድረግ የመክፈት ስራ እንደሚከናወን ተጠቁሟል፡፡
የልማት ስራው የሳይክል፣ አረንጓዴ ስፍራ፣ መዝናኛና የህዝብ መፀዳጃ ስፍራዎችን ያካተተ ሆኖ በሶስት ምዕራፍ እንደሚጠናቀቅ ተመላክቷል፡፡
በመቅደስ አስፋው