የአማዞን ደን ተቆርቋሪው እና የአካባቢው ማህበረሰብ መሪ በኮሮና ቫይረስ ህይወቱ አለፈ
አዲስ አበባ፣ሰኔ 11 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የአማዞን ደን ተቆርቋሪው እና የአካባቢው ማህበረሰብ መሪ የ65 ዓመቱ ፑአሊንሆ ፒያካን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወቱ አልፏል።
በብራዚል ለኮቪድ -19 ወረርሽን ተጋላጭ የሆኑ በአማዞን የሚኖሩ የአገሬው ተወላጅ ማህበረሰቦችን በከባድ ሁኔታ መጎዳቱ ይነገራል።
በዚህም ፑአሊንሆ ፒያካ የአማዞን ደን ጠባቂና ተከራካሪ ከመሆኑም ባለፈ የአገሬው ተወላጅ የሆኑት የካያፖ ህዝብ መሪ የነበረ ሲሆን ÷ፓያካን ረቡዕ ዕለት በሰሜን ፓራ ግዛት ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ህይወቱ ማለፉ ተነግሯል።
ፒያካን በዓለም አቀፍ ደረጃ ትኩረትን የሳበው በፈረንጆቹ በ 1980ዎቹ ሲሆን÷በዓለም ሶስተኛውና ትልቁ የብራዚል ቤሎ ሞንቴ የውሃ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግድብን በተቃወመበት ወቅት ነው።
ፓያካን በ 1980 ዎቹ ብራዚል ወደ ዲሞክራሲ ስትመለስ የአገሬው ተወላጅ ድምጽ በመሆን ለማህበረሰቦቹ በአማዞን ውስጥ ትላልቅ ቦታዎች እንዲኖራቸው ዘመቻውን በመምራት ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል ነው የተባለው ።
ከዚም ባለፈ ህገ ወጥ ማዕድን ቆፋሪዎችን እና ደን መንጣሪዎችን ከአካባቢው ለማስወጣትም መታገሉ ይነገራል።
የአማዞን አካባቢያዊ ፕላኔት ቡድን መሥራች የሆኑት ጌት-ፒተር ብሩክ ለአሜሪካ የዜና ወኪል እንደገለጹት ÷”የአማዞን ደንን ለማዳን እና በአገሬው ተወላጆች ዙሪያ ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን ለመገንባት ዕድሜውን ሁሉ ሠርቷል” ብለዋል።
”እርሱ ከዘመኑ የቀደመ ነው በህልፈቱ ምክንያት እጅግ ጠቃሚ የሆኑ መመሪያዎቹን አጥተናል ”ብለዋል ።
ፓያካን በ1998 አንድ የ18 ዓመት ተማሪን አስገድዶ በመድፈር ጥፋተኛ የተባለ ሲሆን ÷ በዚህም የ 6 ዓመት እስራት ተበይኖበት ነበር።
በወቅቱ ባለቤቱም በጥቃቱ ተባብራለች በሚል ጥፋተኛ መሆኗ ተገልጾ ነበር ፡፡
በወቅቱም አጋሮቻቸው ክሱ ስሙን ለማጠልሸት እና ዝም ለማሰኘት የተቀነባበረ ነው ሲሉ ተከራክረዋል።
ብራዚል ከአሜሪካ ቀጥሎ ከ955 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎቿ በበሸታው የተያዙ ሲሆን – እና ከ 46ሺህ 500 በላይ የሚሆኑት ደግሞ በበሽታው ሞተውባታል።
ምንጭ፡-ቢቢሲ
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።